loading
የሴቶች ሹመት አሁንም ቀጥሏል

የሴቶች ሹመት አሁንም ቀጥሏል

አርትስ 16/02/2011

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት አዲስ ሴት ፕሬዝዳንት መርጧል፡፡

ትላንት በተካሄደው  እና አንድ ሺ 50 አባላት ድምፅ በሰጡበት የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ምርጫ  ሁለት ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን  ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጥ 419 ድምፅ በማግኘት የንግድምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ወ/ሮ መሰንበት የቀድሞ የዓባይ ባንክ ፕሬዚዳንት የነበሩ ሲሆን አሁን የኒው ዳይሜንሽን የንግድ ሥራ አመራር አማካሪ ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡

ንግድ ምክር ቤቱን  አቶ ኤልያስ ገነቲን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *