የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ዜግነት በቃኝ አሉ ፡፡
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ዜግነት በቃኝ አሉ ፡፡
ፕሬዝዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ አሜሪካ የሰጠቻቸውን ዜግነት በፈቃዳቸው መሰረዛቸውን ቢናገሩም ለምን እዚህ ውሳኔ ላይ እንደደረሱ ግን ይፋ አላደረጉም፡፡
ፋርማጆ ጉዳዩን ከጠበቆቻቸው ጋር በመሆን መጨረሳቸውን ከፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት የወጣ መረጃ ያሳያል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የሶማሊያ ህገ መንግስት ጥምር ዜግነት የሚፈቅድ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ግን ሁለቱንም ዜግነት ይዘው መቀጠል አልፈለጉም፡፡
ረዘም ላለ ጊዜ ኑሯቸውን በአሜሪካ ካደረጉ በኋላ ተመልሰው ሀገራቸውን እያገለገሉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ በቀጣዩ ምርጫም ዳግም መፎካከር እንደሚፈልጉ ተነግሯል፡፡
ፋርማጆ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የሀገሬን ህዝብ በማገልገሌ ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፤ሶማሊያዊያን ሀገራችንን ተባብረው ዳግም ታላቅ እንደሚያደርጓት አልጠራጠርም ብለዋል፡፡
ፋርማጆ ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት ማገልገል ከጀመሩ ወዲህ ከአልሸባብ ጋር በሚያደርጉት ውጊያ አሜሪካ ከጎናቸው አልተለየችም፡፡
መንገሻ ዓለሙ