loading
የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት የአገራቱን የሻከረ ግንኙነት እንደሚያስተካክለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት የአገራቱን የሻከረ ግንኙነት እንደሚያስተካክለው ተገለጸ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በዚህ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሻከረውን የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማስተካከል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡ አምባሳደር ዲና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነት ታሪካዊ ነው፤ የሕዝቦች ወዳጅነት የቆየ ከመሆኑም በላይ እጥፍ ድርብ መሆኑን አንስተዋል።


አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወደ ውጭ አገር ሲወጣ ሱዳንን እንደማረፊያ ተጠቅሞ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በተለያዩ ችግሮች ከዚህ ቀደም ከአገር ለሚወጡ ኢትዮጵያውያኖች ሱዳን ማረፊያ ስትሆን እንደነበር አስታውሰው፤ ሕዝቡም ደግሞ ደግና ጨዋ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የሱዳን ወታደራዊ አመራር የሚሠራውን ሥራ የሱዳን ሕዝብን አይወክልም ስንል የነበረው ሕዝቡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መልካም ግንኙነት ስላለው ነው፤ በኢትዮጵያ በኩልም ግንኙነቱን ለማሻሻል
ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


በሌላ በኩል በቅርቡ የሚካሄደው የአፍሪካ የመሪዎችን ጉባዔ ለማስተናገድ ጥሩ ዝግጅቶች እየተደረገ ነው ያሉት አምባሳደር ዲና ፤ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከኢሚግሬሽን ፣ ከጸጥታ ጉዳይና ከመስተንግዶ ጋር በተገናኘ የተሳካና ሰላማዊ ቆይታ እንዲሆን እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ በሳዑዲ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎችን በተመለከተ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ከታዋቂ ሰዎች የተውጣጡ ተውካዮች ወደ ሳዑዲ ለማቅናት ቪዛ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፤
መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ጥረቶችን እያደረገ ነው፤ ተወካዮች ወደ ሳዑዲ አምርተው የተቸገሩ ዜጎችን ወደ አገር እንዲመለሱ ያደርጋሉም ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *