loading
የቀድሞው አፈ-ጉባኤ አምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ የቀብር ስነ-ስርዓት የፊታችን እሁድ ይፈጸማል

የቀድሞው አፈ-ጉባኤ አምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ የቀብር ስነ-ስርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስታወቀ  ፡፡

የአምባሳደር ዳዊት ዮሀንስ አስክሬን ከአሜሪካ ኒዮርከ ከተማ የስንብትና የአሸኛኘት ፕሮግራም የተደረገለት ሲሆን ቅዳሜ ጥር 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡30 በኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚደርስ ተገልጿል፡፡ በቦታው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ቤተሰቦች በመገኘት አቀባበል እንደሚደረግም ምክር ቤቱ ለአርትስ ቲቪ የላከው መግለጫ ያስረዳል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *