loading
የብሔራዊ ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ

በዛሬው ዕለት ሁለት ግጥሚያዎች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

ምሽት 4፡45 ጀርመን በወልፍስቡርግ ቮልስዋገን አሬና ላይ ሰርቢያን ታስተናግዳለች፡፡

በአሰልጣኝ ዩአኪም ሎው የሚመራው የጀርመን ቡድን በብራዚል የተሰናዳውን የዓለም ዋንጫ ቢያሳኩም፤ በሩሲያው መሰናዶ ገና በጊዜ ነበር የተሰናበቱት፤ በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ውድድርም ቢሆን አልሆነላቸውም፡፡

ከውጤት ማጣት ጉዞዎች በኋላ ጀርመን የዩሮ 2020 የማጣሪያ ውድድሯን ከመጀመሯ አስቀድሞ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ታደርጋለች፡፡

የማንችስተር ሲቲው አማካይ ኢልካይ ጉንዶጋን ከመስከረም ወር በኋላ ወደ ቡድኑ የተመለሰ ሲሆን አሰልጣኝ ሎው ማኑኤል ኑዬር አሁንም ተቀዳሚ ግብ ጠባቂያቸው እንደሆነና ማትስ ሁመልስ፣ ቶማስ ሙለር እና ጄሮም ቦአቲንግን ማሰናበታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰርቢያ በቡንደስሊጋው የሚጫወቱ አራት ተጫዋቾች ያሏት ሲሆን የአይንትራክት ፍራንክፉርቱ ሉካ ዮቪች በውድድር ዓመቱ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል፡፡

ሌላኛው የፉልሃሙ አጥቂ አሌክሳንደር ሚትሮቪችም ቢሆን የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ነው፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን 28 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ጀርመን በ16ቱ ላይ የበላይነት አላት፤ ሰርቢያ 8ቱን ስታሸንፍ በአራቱ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 4፡45 ላይ ዌልስ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ሬክሰም ከተማ በሚገኘው ሬስኮርስ ግራውንድ ስታዲየም ትሪንዳድ እና ቶቤጎን ትገጥማለች፡፡

በቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሪያን ጊግስ የምትሰለጥነው ዌልስ ከዩሮ 2020 የማጣሪያ ጨዋታዎች በፊት የምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ለቡድኑ ማነቃቂያ ይሆናል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *