loading
የብሩንዲ ህገ መንግስታዊ ርድ ቤት የሀገሪቱን የምርጫ ውጤት አፀና ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2012 የብሩንዲ ህገ መንግስታዊ ርድ ቤት የሀገሪቱን የምርጫ ውጤት አፀና ::ፍርድ ቤቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረቡትን የምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል የሚል ቅሬታ ውድቅ በማድረግ ኢቫሪስት ንዳይሺሚ አዲሱ የብሩንዲ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ የዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አጋቶን ሩዋሳ ባቀረቡት ቅሬታ ንዳይሺሚ በ68 በመቶ የድምፅ ብልጫ አሸንፈዋል መባሉን ፈጽሞ የማንቀበለው ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቱ ናሽናል ፍሪደም ካውንስል የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ የምርጫ ውጤቱ ስለመጭበርበሩ በቂ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ያልተቀበሉት ሩዋሳ ጉዳዩን ወደ ምስራቅ አፍሪካ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት
ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ የ52 ዓመቱ እና የቀድሞው የጦር ጄኔራል የነበሩት ንዳይሺሚ ብሩንዲን ለ15 ዓመታት በመሩትና
ከእንግዲህ በቃኝ ብለው ስልጣናቸውን በለቀቁት ፕሬዚዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ አቅራቢነት ነበር በምርጫው የተወዳደሩት፡፡ የምእራባዊያን ዲፕሎማቶች በጋራ በሰጡት መግለጫ ምርጫው ብዙም መሰናክሎች እንደዳልታዩበት ገልፀው ቅሬታ ካለ እንዲህ በህጋዊ መንገድ መቅረብ አለበት ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *