loading
የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ::

የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ  ድጋፍ ያደረጉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡ድጋፉ በዋነኝነት ለኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ተግባር የሚውሉ ሲሆን 280 ካርቶን ወይም 1 ሺህ 700 ኪሎ ግራም የሆነ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ የኬሚካል ማጽጃዎች፣ የማጽጃ አልባሳት እና ሌሎችም ቁሳቁሶች ይገኝበታል፡፡

የቁሳቁስ ርክክቡ በተካሄደበት ወቅት በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ሚስትረስ ያፕላክ አልፕ በሁለቱ አገራት መካከል በባህል፣ በታሪክና በዲፕሎማሲው መስክ የቆየ ወዳጅነት መኖሩን አስታውሰው በኢኮኖሚው ረገድም የአገሪቱ ኢንቬስተሮች በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፤ የቱርክ መንግስት በዚህ አስከፊ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን በመሆን ላደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ አመስግነው ይህም በአገራት መካከል የጠበቀ ግንኙነት ለመኖሩ ትልቅ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ድጋፉ ወረርሽኙን ለመከላከል እንደ አገር እየተደረገ ላለው ርብርብም የበኩሉን እገዛ እንደሚያደረግ ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *