loading
የቱርክ ባለሃብቶች በትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው

አርትስ 21/02/2011

 

የቱርክ ባለሃብቶች በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አደ ጉደም ከተማ በ750 ሚሊየን ዩሮ ስለሚገነቡት የኢንዱስትሪ ፓርክ ከከተማ አስተዳደሩናከተለያዩ የህብረተሰብ  ክፍሎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ በመጭው መጋቢት ወር እንደሚጀመር እና  በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ነው የተነገረው፡፡

የሕንጣሎ ዋጀራት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከለሌ ሓጋዜ  ኢንዱስትሪ ፓርኩ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የመሬት ርክክብና ሌሎችአስፈላጊ ነገሮችን ለሟሟላት መዘጋጀታቸውን  ገልፀዋል።

ፓርኩ በ500 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፥ ወደ ስራ ሲገባ በዓለም ተወዳዳሪና አዲስ ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ነው የሚጠበቀው፡፡

ከዚህ ባለፈም ፓርኩ የሚገነባበት አካባቢ ለመቐለ ከተማ ያለው ቅርበት የቱርክ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ እንዲመርጡት እንዳደረገው ነው አስተዳደሪው የገለጹት ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *