loading
የቱርክ ተዋጊ ጄቶች በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኘው የፒኬኬ የጦር ሰፈር ድብደባ ፈጸሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2012  የቱርክ ተዋጊ ጄቶች በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኘው የፒኬኬ የጦር ሰፈር ድብደባ ፈጸሙ፡፡የጦር ጄቶቹ ከቱርክ የተለያዩ የአየር ሃይል ማረፊያዎች በመነሳት የፒኬኬ ዋነኛ የጦር ካምፕን ጨምሮ በሰሜናዊ ኢራቅ የሚገኙ በርካታ ስፍራዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል፡፡እንደ ሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ከሆነ የጦር ድብደባው በቱርክ የጦር ካምፕ ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው የተወሰደ የአፀፋ እርምጃ ነው፡፡የቱርክ መከላከያ ሚኒስትር በቲዊተር ገጻቸው የጥቃቱ ዋነኛ ኢላማ የአሸባሪዎች ምሽግ በሆኑ ዋሻዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ነው ብለዋል፡፡ለአልጄዚራ ከኢስታንቡል የሚዘግበው ሲኔም ኮሴግሉ የአየር ጥቃቱ ከተለያዩ የአየር ሃይል ማረፊያዎች የተነሳ በቅንጅት የተመራ ነው ብሎታል፡፡እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1984 ፒኬኬ የቱርክን መንግስት ተቃውሞ ጦር ማንሳቱን ተከትሎ በቱርክ መንግስት፣ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት ሽብርተኛ ተብሎ መፈረጁ የሚታወስ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *