loading
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ድርድረ በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሄደ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ድርድረ በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሄደ፡፡ዉሃ መስኖና እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በበይነ-መረብ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ታዛቢዎች በተገኙበት በውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ተካሂዷል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር በሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ታዛቢዎቹም ደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በተገኙበት ነዉ የተካሄደዉ፡፡በዚህ ስብሰባ ሀገራቱ የድርድር ስነ-ስርዓትን/procedure፣ ታዛቢዎችን፣ ስለ ድርድሩ አካሄድ እና ዋናዋና የድርድር ያልተቋጩ ጉዳዮችን በተመለከተ ተነጋግረዋል።

እያንዳንዱ ሀገር ዋናዋና የድርድር ጉዳዮች ናቸው ያሏቸውን ሃሳቦች በዝርዝር አቅርበዋል። በዚህም መሰረት በቀጣይ ቀናት ተከታታይ ውይይቶችን ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።ይሁን እነጂ የታዛቢዎቹ ሚና ምን ይሁን የሚለውን በተመለከተ በሀገራቱ መካከል መግባባት ላይ ያልተደረሰ ሲሆን ስብሰባው በዛሬው ዕለትም የሚቀጥል ይሆናል።የሶስቱ ሀገራት ድርድር የግድቡ የመጀመሪያ ሙሌት እና ዓመታዊ አለቃቅ ላይ ብቻ የተወሰነ እንደሚሆን ሚኒስቴሩ የገለጸ ሲሆን ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ልዩነቶችን በድርድር ለመፍታት ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዝግጁ መሆንዋን ሚኒሰቴሩ ገልጿል፡፡

ምንጭ፤-የዉሃ መስኖና እና ኢነርጂ ሚኒስቴር

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *