loading
የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ትምህርታዊ ዝግጅቶችን በኢትዮሳት የቴሌቪዥን መድረክ ማስተላለፍ ጀመረ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ትምህርታዊ ዝግጅቶችን በኢትዮሳት የቴሌቪዥን መድረክ ማስተላለፍ ጀመረ ::ሚኒስቴሩ ከዩኒሴፍና ከሕፃናት አድን ድርጅት ጋር በተባበር ነው ትምህርታዊ ዝግጅቶቹን የጀመረው፡፡ በኢትዮጵያ ለትምህርት ማሰራጫ የታለመው የመጀመሪያው የሳተላይት መድረክ ኢትዮሳት በኮቪድ 19 ምክንያት የተቋረጠውን የትምህርት ቤቶች የትምህርት ተግባር ለማሰቀጠል እንዲቻል ዘጠኝ ትምህርታዊ ቻነሎችን በስርጭቱ ሥርዓት ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓል፡፡ የነዚህ ዝግክቶች መጀመር ዓላማ በአለም የግኑኝነት ወይም የመገናኛ መፍትሄዎች መሪ በሆነው SES በተሰኘው ድርጅት ድጋፍ በኮቪድ 19 ምክንያት የተቋረጠውን የት/ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደትን ማሰቀጠል ነው፡፡ ዝግጅቶቹ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች በ8 ቋንቋዎች የሚያስተለልፉ የትምህርት ጣቢያዎቸ ከግንቦት 24 ቀን 2012 ጀምሮ በ SES’ ኤን ኤስ ኤስ-12 57 ዲግሪ ኢስት ላይ በሚገኘው በኢትዮሳት የሳተላይት መድረክ ብቻ ይተላለፋሉ፡፡ ኮቪድ19 በትምህርት ላይ ላስከተለው ችግር ምላሽ የመስጠት ዕቅደ ዋነኛ አካል የሆነው ይህ ዝግጅት በሀገራችን በትምህርት ላይ ላሉ ሕፃናት በርቀት ትምህርት ሁነኛ መፍትሄ ይሰጣል ብሏል የትምህርት ሚኒስቴር፡፡ ከአዲሶቹ የቴሌቭዥን ቻነሎች መካከል ስምንቱ አገልግሉት በሚሰጡባቸው ክልች አማካይነት የሚሰየሙ ሲሆን አንዱ ጣቢያ ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር ስር ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ድጋፉ ትምህርት ቤቶች ቢዘጉም ተማሪዎች ከትምህርት እንዳይለዩ እንዲሁም ኮቪድ19 ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ወደፊትም የሚያጋጥሙትን ሌሎች ችግሮች የመቋቋም አቅሙን የሚያጠናክር ይሆናል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *