loading
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከደቡብ ክልል የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከደቡብ ክልል የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው፡፡ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ፥ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በትምህርት ዘርፍ የገዘፈውን የጥራት መጓደል ለመፍታት ይሰራል።


በኢትዮጵያ ለትምህርት ተደራሽነት የተሰጠውን ትኩረት ያህል ለጥራቱ ያለመጨነቅ ፣ የትምህርት ዘርፉ ከፖለቲካ ጋር መደበላለቅ፣ ትምህርት እና ብሔርተኝነት፣ የግብረገብነት ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ለትምህርት ዘርፉ የጥራት ማነስ መንስዔ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቻችን እየተሰጠ ያለው ትምህርት የተማሪዎችን ብቃት የሚመዘንበት አይደለም ሲሉም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ተናግረዋል ።
በቀጣይ የመምህራንን አቅም ማሳደግ፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም ትምህርትን ከፖለቲካ ነጻ ማድረግ ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።


እንደ ፕሮፌሰሩ ገለጻ ፥ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ባደረገው ወረራ በአማራና አፋር ክልሎች 1ሺ85 ትምህርት ቤቶች ማፍረሱን ጠቁመዋል። በዚህም የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ የመገንባት ስራ ይሰራል ሲሉም ጠቁመዋል። ሚኒስትሩ ከውይይቱ በተጨማሪ በክልሉ የተመረጡ ትምህርት ቤቶችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *