loading
የትግራይና አማራ ክልል እግር ኳስ ክለቦች ሰላማዊ የሆነ ጨዋታ ያደርጋሉ ተባለ

አርትስ ስፖርት 14/03/2011

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በትግራይና አማራ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች መካካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች ሲራዘሙ በገለልተኛ ሜዳ ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ በ2011 የዉድድር መርሀ ግብሮች ያለ ዉከትና ብጥብጥ ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲተገበሩ የስፖርት ኮሚሽን እና የክልል አመራሮችከስፖርት ማህበራት ጋር በቅንጅት ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

የባህልና ቱሪዝም  ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ፤ ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል እና ከአማራ ክልል  ርዕሰ መስተዳድር አቶገዱ አንዳጋቸው ጋር በሁለቱም ክልሎች የሚካሄዱ ዉድድሮች ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሰዉ በሚካሄዱበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።

ዶ/ር ደብረፂዮን ህዝቡ በክልሉ የሚካሄዱ የስፖርት ዉድድሮች በተለመደዉ የእንግዳ አቀባበል ባህል መሠረት ለማስተናገድ ዝግጁ  መሆናቸዉንአረጋግጠዋል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በክልሉ የሚካሄዱ ውድድሮች እጅግ ሰላማዊ ሆነው እንዲካሄዱ የክልሉ ህዝብና መንግስት ፍላጎት እንደሆነ ገልፀው ከዚህበኋላ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር እንዳይከሰት በትኩርት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ስፖርት ኮሚሽን እንደገለፀው ስፖርት ያተለመለትን ዓላማ ይዞ መቀጠል የሚችለዉ ህጉንና ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከናወን ጉዳዩ በሚያገባዉአካል ጥበቃ ሲደረግለት ነዉ ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *