loading
የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያጸኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አይደለም፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 14፣2013 የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያጸኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የውስጥም ሆነ የውጭ ሀይሎች ሲንቀሳቀሱ የትግራይ ህዝብ የመጀመሪያ ከለላ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በቦሌ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ደም በመለገስ ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

ዶክተር አብርሃም በላይ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለራሱ ጥቅም ሲል ብቻ ህፃናትን ከመማገድ ጀምሮ የጦር ወንጀል እየፈፀመ ሲሆን ይህ የቡድኑ የሽብር ድርጊት የትግራይ ህዝብን አይወክልም ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚያፀኑ እንጂ የሚያፈርሱ ሀይሎች አካል አይደሉም ሊሆኑም አይችሉም
ነው ያሉት። የአሸባሪው ቡድን ድርጊት የትግራይን ህዝብ ባህል፣ ታሪክ እና እምነት የማይመጥን እና የማይወክልም ነው ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *