loading
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝቦች ሉአላዊነት መከበር ያበረከተውን  አስተዋጽኦ አደነቁ

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝቦች ሉአላዊነት መከበር ያበረከተውን  አስተዋጽኦ አደነቁ።

 

መከላከያ ሰራዊቱ ለልማትና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የህገ-መንግስትና የህዝቦች ሉአላዊነት ያለምንም መሸራረፍ እንዲከበር በማድረግ አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነ ነው ብለዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሃገር መከላከያ ሰራዊት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የሀገራችንና ጎረቤት ሀገራት ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ የሰራቸው ስራዎች ከሀገራዊ ፋይዳው አልፎ ዓለም አቀፍም አርአያነትም ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰራዊቱ በአፍሪካ ሃገራት የተፈጠሩ ግጭቶችን ለማረጋጋት በተሰማራበት ሁሉ በድል ማጠናቀቁ የህዝባዊነቱ እና የዓላማ ፅናቱ ማሳያ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝቦች ሉአላዊነት መከበር  እንዲሁም ለፍትህና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላበረከተው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን በመግለጽ አመስግነዋል፡፡

መከላከያ ሰራዊቱ የሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ወዳድ ህዝቦች አለኝታ እንደሚሆን በመተማመን የትግራይ ህዝብና መንግስት ከጎኑ ይቆማል ነው ያሉት።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *