የቻይና የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እፈልጋለሁ አለ
በእስያ ትልቁ የኤሌክትሮኒክስ አምራች የሆነው የቻይና የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ በከተሞች ዝመና እና በዜጎች ደህንነት ጥበቃ ላይ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
የቻይና የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ምክትል ፕሬዝደንት ሊ ሊጎንግ በኢትዮጵያ የከተማ ዝመና ‹‹ስማርት ሲቲ››፤ በዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር እና በዜጎች ደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብተዋል።
ኩባንያው ይህንን ይፋ ያደረገው
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የተመራ ልኡክ የቻይና ኩባንያውን ከጎበኘ በኋላ ከተቋሙ ኃላፊዎች ጋር ምክክር ባደረገበት ወቅት ነው።
ሚኒስትሩ በዚሁ ውይይት ላይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ ቻይና የምትዘረጋው ቴክኖሎጂ በቀላሉ ለአፍሪካውያን የመታየት እድል ስለሚኖረው እድሉን እንዲጠቀሙበት ነው የኩባንያውን ሃላፊዎች የጠየቁት።