የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ::
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ:: ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይቅርታ የጠየቁት ብሪንተን ታራንት የተባለው ትውልደ አውስትራሊያዊ ወጣት ያደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ ከጦር መሳሪያ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ስህተት ነበር በማለት ነው፡፡
የሀገሪቱ የወንጀል መርማሪ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ፖሊስ ግለሰቡ የጦር መሳሪያ ፈቃድ ሲሰጠው አስፈላጊውን ማጣራት አላደረገም ሲል ተችቷል::
ኮሚሺኑ ቀድሞ መረጃ ባለማግኘቱ ምክንያት በእምነት ቦታቸው የተገኙ ወገኖቻችን በግፍ ተገድለዋል ለዚህም ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው የሀገሪቱ የደህንነት ተቋማት አብዝተው የተወቀሱት ታራንት የነጭ የበላይነትን መሰረት ያደረገ የግድያ ማኒፌስቱ በማህበራዊ ድረ ገፁ መልቀቁን ከግምት አስገብተው ልዩ ክትትል ባለመድረጋቸው ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ በወቅቱ የትኩረት አቅጣጫቸው በአክራሪ ሙስሊም የሽብር ቡድኖች ላይ በማድረጋቸው ነው የተዘናጉት የሚል ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ተከሳሹ ብሪተን ታራንት በ50 ሰዎች ግድያ፣ 40 ሰዎችን በማቁሰልና በሽብር ወንጀሎች ተከሶ ጥፋተኛ
መባሉን ተከትሎ ያለ ይግባኝ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል፡፡