loading
የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ::

የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ::

የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ቦርዶች ለሀገራት እና ኩባንያዎች ለለኮቪድ -19 መስፋፋት ለመከላከል ፣ ለመለየት እና ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ጥረት 14 ቢሊዮን ዶላር ለፈጣን ቁጥጥር ፋሲሊቲ እንዲጨምር ፈቀደ ፡፡በሳምንቱ መጨረሻ የዓለም ባንክ ለፈጣን ቁጥጥር 1ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በ 40 አገሮች ውስጥ ፕሮጀክቶችን እያዘጋጀ ነውም ተብሏል፡፡ በአፍጋኒስታን እና በኢትዮጵያ የሚሰሩ እንቅስቃሴ እጅግ የላቁ ስለሆኑ በሚቀጥለው ሳምንት ለቦርዱ ቀርበው ይጸድቃሉ ተብሏል ፡፡ የሌሎች 14 አገራትም ውሳኔዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይታያሉ፡፡

ከአዲሱ በጀት በተጨማሪ አሁን ያሉትን ፕሮጀክቶች መልሶ ማቋቋም የ ኮቪድ-19 ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ፡፡ እስካሁን ድረስ እስከ 1ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በ 24 አገራት ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ናቸው ፡፡  የኮቪድ 19 መስፋፋትን ለመግታት ፣ ክትባቶችን ለማዳበር እና ለወረርሽኝ ዝግጁነት ከ ቡድን 20 ድጋፍ ሰጪ ድርጅት፣ አይ ኤም ኤፍ ና ከቢል ጌትስ ፋውንዴሽን  ጋራ አብረን በትብብር እየሰራን ነውም ብሏል፡፡ ሰራተኞቻችን ወደ ቤት ተኮር ስራ አዛውረናል ያለዉ ድርጅቱ ፡ ሽግግሩ ፈታኝ ነው ቢሆንም በአስቸኳይ እንቅስቃሴዎች ትኩረታቸውን ለመቀጠል የሰራተኞቻችን አቅም መሻሻልና በግንኙነት ቴክኖሎጂ ተደስተናል ብሏል፡፡   ይህንን ቀጣይነት ያለው ቀውስ ለመቅረፍ በትጋት እና በትዕግስት ለሚሰሩ በዓለም ዙሪያ ላሉት ሰራተኞቹ ምስጋናውን እቅርቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *