loading
የአልጀሪያው ፕሬዚዳንት የኮቪድ-19 ህክምናቸውን አጠናቀቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 የአልጀሪያው ፕሬዚዳንት የኮቪድ-19 ህክምናቸውን አጠናቀቁ::ባለፈው ኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ ተመርምረው ቫይረሱ እንዳለበባቸው ያወቁት ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ቲቦኒ ለህክምና ክትትል ወደ ጀርመን ተጉዘው ነበር ተብሏል፡፡ ቲቦኒ ከዚህ በኋላ ተበቤተ መንግስታቸው ሆነው ጨማሪ የህክምና ክትትሎች እንደሚደረጉላቸው ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ያሉበትን ሁኔታ አስመልክተው ለዘህዝቡ መግለጫ እንዲሰጡ ቢሯቸው ወስኗል፡፡ ቲቦኒ በመጀመሪያ በሽታው እንደተገኘባቸው ወደ ጦር ሓይሎች ሆስፒታል ተወስደው አስፈላጊው የባለሙያዎች እገዛ ተደርጎላቸዋል፡፡ አልጀሪያ እስካሁን ከ2 ሺህ በላይ ዜጎቸዋ በኮሮናቫ ቨይረስ ሳቢያ የሞቱባት ሲሆን ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል፡፡

የቅርብ ሰዎቻቸው እንሉዳት ከሆነ ፕሬዚዳንቱ ቀሪ ምርመራዎችን እንዳጠናቀቁ ስራቸው ላይ ለመገኘት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የፕሬዚዳንቱ ታሞ ሆስፒታል መግባት በርካታ አልጀሪያዊያንን የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብደልአዚዚ ቡተፍሊካን ሁኔታ እንዲያስታወሱ አድርጓቸዋል ሲሉ የገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *