loading
የአማራ እና ቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤቶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የአማራ እና ቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤቶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

አርትስ 10/03/2011

 በአጎራባች ወረዳዎች ዘላቂ ሰላም ለመፈጠር፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት እና በፖለቲካዊ ዘርፎችም በጋራ ለመሥራት ስምምነቱ ተፈርሟል፡

ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ፣ አሠራሮችን በማሻሻል ለወከሉት ሕዝብ በግልጽነትና በተጠያቂነት ለማገልገል፣ የተጀመረውን ለውጥም አጠናክሮ ለማስቀጠል ነው ስምምነቱን የአማራና ቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤቶች ትናንት የተፈራረሙት፡፡

የጋራ መድረክ በመመሥረትም በዓመት ሁለት ጊዜ እየተገናኙ ለመምከር ምክር ቤቶቹ ስምምነት አድርገዋል፡፡ ስምምነቱ አንድ የጋራ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚደረገውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት መሆኑም ተነግሯል፡፡

አብመድ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *