የአሜሪካው የቦይንግ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጋር ውይይት አደረገ
የአሜሪካው የቦይንግ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጋር ውይይት አደረገ
አርትስ 12/03/2011
አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከአሜሪካው የቦይንግ ካምፓኒና ከታላቋ ሲያትል አጋር ድርጅት ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂዷል ተባለ፡፡
በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ኢትዮጵያና አሜሪካ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፉ ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከድርጅቶቹ የስራ ሃላፊዎች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡
እንደውጭ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ገለፃ የኢትዮጵያ ቢዝነስ ምክር ቤትን በአሜሪካ ሲያትል ለማቋቋም ቦይንግ ኩባንያ እና የታላቋ ሲያትል አጋር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
የታላቋ ሲያትል አጋር የአሜሪካ ሲያትል ከተማን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የተቋቋመ የመንግስት እና የግል የጋራ ድርጅቶች ጥምረት ሲሆን ቦይንግ ኩባንያ ደግሞ787 ዲሪም ላይነር እና ቦይንግ – 777ን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በማምረት እና ለዓለም ገበያ በማቅረብ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ኩባንያ ነው፡፡