የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አበረከተ::
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ
አበረከተ:: ዓለም አቀፉ የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አበረከተ።
ዩ.ኤስ.ኤይድ ኢትዮጵያ በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው፥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ባለበት በዚህ ወቅት ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር የመመርመር አቅመን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። በዚህም መሰረት ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ማበርከቱን የገለፀ ሲሆን፥ ድጋፉም የኢትዮጵያን የምርመራ አቅምን ያሳድጋል ብሏል። የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶቹ አዲስ አበበን ጨምሮ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ በተዛመተባቸው አካባቢዎች እንደሚውልም አስታውቋል።