loading
የአሜሪካ ሳይንቲስቶች አሁንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ትልቅ ፈተና ነው ሲሉ አስጠነቀቁ::

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 የአሜሪካ ሳይንቲስቶች አሁንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ትልቅ ፈተና ነው ሲሉ አስጠነቀቁ::
የአሜሪካ የበሽታዎች መቀጣጠርና መከላከል ማእከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሮበርት ሬድፊልድ ወረርሽኙ ሀገሪቱንአንበርክኳታል በማለት ነው የሁኔታውን አስከፊነት የገለፁት፡፡የዋይት ሀውስ የኮቪድ 19 መከላከል ግብረ ሀይል ሀላፊና የተላላፊ እና ኢንፌክሽን ህመሞች ኤክስፐርት የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውችም ይህንኑ ሀሳብ እንደሚጋሩት ተናግረዋል፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን ባለሞያዎቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ቫይረሱ ካደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ በተጨማሪ ገና በርካታ ትሪሊዮን ዶላሮችን በማስወጣት ኢኮኖያዋንም በእጅጉ ይጎዳዋል፡፡ ክትባትን በተመለከተ ተስፋ ቢኖርም ገና ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ መዘናጋት አያስፈልግም ሲሉም
ሞያተኞቹ አስጠንቅቀዋል፡፡ ዶክተር ፋውቺ ምርመራ ይቀንስ የሚለው የፕሬዚዳንት ትራምፕ ሀሳብ ችግር አይፈጥርም ወይ ተብለው ተጠይቀው በሰጡት መልስ እንዲህ አይነት ቀጥተኛ ትእዛዝ አልደረሰንም ምርመራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደ ቴክሳስ፣ ፍሎሪዳ፣ እና አሪዞና ባሉ ግዛቶች የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ መጠን መጨመር ማሳየቱ ስጋትን ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *