loading
የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሀላፊ ስልጣናቸውን ለቀቁ፡፡

የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሀላፊ ስልጣናቸውን ለቀቁ፡፡

የደህንነት ሀላፊዋ ስራ የመልቀቃቸው ምክንያት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሚከተሉት የስደተኞች ፖሊሲ ጋር የተያያዘ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ትራምፕ  የሀገር ውስጥ ደህንነት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን የክርስቲን ኔልሰንን ቦታ በጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ ኮሚሽነሩ ኬቨን ማካሊና የመተካት ሀሳብ አላቸው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከአሁን ቀደም በኔልሰን ደስተኛ እንዳልሆኑ እና በሌላ ሰው ሊተኳቸው እንዳሰቡ ተናግረው ነበር ተብሏል፡፡

ለዚህ አባባላቸው ያቀረቡት ምክንያት ደግሞ ኔልሰን እኔ በማስበው ልክ ጠንካራ አይደሉም የሚል ነው፡፡

ይሁን እንጂ  ኔልሰን የትራምፕን ፖሊሲ በማስፈፀም እናት እና ልጅን በመለያየት ሀላፊነት አለባቸው ከሚል ከበርካቶች ትችት አላመለጡም፡፡

የደህንነት ሀላፊዋ ለመልቀቃቸው የትራምፕ ግፊት እንዳለበት ብዙዎቹ ቢናገሩም እሳቸው ግን ምክንያታቸውን በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

ሆኖም  አሜሪካ እኔ ወደዚህ ስራ ከመግባቴ በፊት ከነበረው በተሻለ ደህንነት ላይ ትገኛለች በማለት በስራቸው ጉድለት እንዳልነበረ የሚያሳይ ሀሳብ በመልቀቂያ ደብዳቤያቸው  ላይ አስፍረዋል፡፡

የኔልሰንን መልቀቅ አስመልክተው የዲሞክራቲክ ፓርቲ ሰዎች ስራቸውን ከጅምሩም ያላማረ እና ውሳኔውንም የዘገየ ሲሉት ከሪፓብሊኩ  ወገን ደግሞ ሴትዮዋ የመርህ ሰው ነበሩ የሚል ሙገሳ ደርሷቸዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *