
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ 123 ሰዎች ሲገደሉ 500 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ::
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ 123 ሰዎች ሲገደሉ 500 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ:: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራውን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ወቅት በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎች ያደረሱት ጥቃት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ባሕርያትን የሚያሟሉ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡