loading
የአስረኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆነ

አርትስ 02/13/2010
ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤጀንሲው በዘንድሮው አመት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጿል።
ከተፈታኞቹ መካከልም 71 ነጥብ 4 ያክሉ ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ሲሆን፥ ከ7 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ አራት ነጥብ ማምጣታቸውንም ነው የገለጸው።
ከውጤቱ ባለፈም ወደ መሰናዶ ትምህርት መግቢያ ይፋ የተደረገ ሲሆን፥ ለወንዶች 2 ነጥብ 71 እንዲሁም ለሴቶች 2 ነጥብ 57 ሆኗል።
ለታዳጊ ክልሎች ለወንድ 2 ነጥብ 43፣ ለሴቶች 2 ነጥብ 29 ሲሆን፥ ለአካል ጉዳተኛ ለወንድ 2 ነጥብ 14 ለሴት ደግሞ 2 ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።
ተፈታኖች ዛሬ ከ12 ሰአት በሃላ በrtn 8181 እና በፈተናዎች ኤጄንሲ ድረ ገጽ http://app.neaea.gov.et/Home/Student ላይ ኮዳቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉም ሀገር አቀፉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ገልጿል።

ኤፍ ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *