loading
የአሸባሪው ጌታቸው ረዳ ወንድም ሃይለ ረዳ መልዕክት፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 14፣2013 አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ እንቅስቃሴ የአገር ክህደት መሆኑን የጌታቸው ረዳ ወንድም ሃይለ ረዳ ገለጹ:: በአፋር ክልል ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ ዜጋ መምህሩ ሃይለ ረዳ፤ አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ን ህዝብ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ደም ለማቃባት ትንኮሳ ማድረጉ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲሉም
ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ የአገር ዳር ድንበር የሚጠብቀውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝን ድንገት በማጥቃት የፈፀመው ዘግናኝ ድርጊትም በየትኛውም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ አላስፈላጊ ግጭትና ጦርነት እንዲካሄድ አሸባሪው ህወሓት ቆርጦ በመነሳት የችግሮች ሁሉ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ የትግራይን ህጻናት ለጦርነት መልምሎ በማሰለፍ ከፍተኛ ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል ነው ያሉት መምህር ሃይለ ረዳ። የግለሰቦችን ስልጣን ለማስጠበቅ ሲባል ህፃናትን ለጦርነት በማሰለፍ ህይወታቸው እንዲቀጠፍ በማድርግ የትግራይ ክልል ነዋሪ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዲገባ እያደረጉት መሆኑን አመልክቷል። በአፋር ጋሊኮማ ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ የሽብር ቡድኑ የፈፀመውን የጭካኔ ተግባርም ማውገዛቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *