loading
የአብን ማሳሰቢያ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 የአገራችንን ምኅዳር ለአንድ ወገን ዘረኛና ያልተገራ ሽምጥ ግልቢያ የሚያመቻቹ ኃይሎች ከወዲሁ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲል አብን አሳሰበ፡፡ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ባወጣዉ መግለጫ፤ የአማራ ሕዝብ በአገዛዙ ላይ የቀረውን ተስፋና በጎ ግምት ሁሉ አስተባብሎ መጨረሱን እና በየቦታው በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋና ፖለቲካዊ አሻጥር በማያሻማ ሁኔታ በአገር ቤትና በውጭ አገር ባካሄዳቸው ሰላማዊ ሰልፎች አውግዟል፤ አጋልጧል ብሏል። ፓርቲዉ በመግለጫዉ ሰልፎቹ እጅግ ሰላማዊና በሰለጠነ መልኩ የተካሄዱ ከመሆናቸው ባሻገር የአማራን ሕዝብ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ለወዳጅም ለጠላትም በግልፅ ያሳዩ ነበሩ ብሏል።

የአማራን ሕዝብ ጅምላ ሞትና መፈናቀል «የተለመደና ነባራዊ» ለማድረግ ከየአቅጣጫው የተከፈተውን ሴራ መመከት የሕዝባዊ ንቅናቄው አንድ ዘርፍ ሆኖ መቀጠል አንዳለበት አብን በጽኑ እንደሚምን ገልጿል፡፤ አማራ በማንነቱ ተለይቶ ተከታታይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሲከፈትበት ለባሕል፣ ለሞራልና ለሕግ ተቃራኒ
መሆኑን ገልፀው ያላወገዙ አካላት ሁሉ የለመዱትን «ማኅበራዊ ሳንሱር» ለማድረግ የያዙት አካሄድ ዘመኑን ያልዋጀና ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ማስገንዘብ ያስፈልጋል ብሏል በመግለጫዉ። አሁንም የአገራችንን ምኅዳር ለአንድ ወገን ዘረኛና ያልተገራ ሽምጥ ግልቢያ የሚያመቻቹ ኃይሎች
ከወዲሁ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ስንል ማሳሰብ እንወዳለን ብሏል።

በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈቱት ጥቃቶች አድማስ ከእለት ወደ እለት እየሰፉና ቅርፃቸውን እየቀያየሩ መምጣታቸውን ሁሉም የሚረዳው ኃቅ ከሆነ ውሎ አድሯል። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ «በአማራክልል» በተለያዩ አካባቢዎች፣ በመሐል ቀጠናዎች ጭምር የተቀናጁ በርካታ ጥቃቶች ተከፍተዋል።
ጽንፈኛው የኦነግ ሸኔ ኃይል በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሔረሠብ ዞን፤ ራሱን «የቅማንት ኮሚቴ» ብሎ የሚጠራው ኃይል በጎንደር ጭልጋ አካባቢ፤ የትሕነግ ናፋቂና ትራፊ ኃይል ደግሞ በዋግ ኽምራ ዞን በህዝባችን ላይ በርካታ ጥቃቶችን መክፈታቸው ተረጋግጧል።

በመሰረቱ እነዚህ በአንድ ላይ በቅንጅት የተከፈቱ ጥቃቶችን በማየት በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠው «የኅልውና አደጋ» መሆኑን ማንም አገር ወዳድ ዜጋ የሚገነዘበው ነው ብሏል በመግለጫዉ፡፤ለአማራ ህዝብ የምርጫ ካርዱን በማዉጣት ፡በምርጫ ካርድዎ የመዋቅርና ሕግ ሰራሽ ችግሮችን ሰንኮፍ ነቅሎ ዲሞክራሲን ማስፈኛ ጊዜው አሁን ነዉ ሲል ጥሪ አቅርቧል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *