loading
የአንድ ሀገር ብልጽግና ከማኅበራዊ ኃላፊነት መጎልበት ጋር ከፍተኛ ትሥሥር አለው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ:

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የአንድ ሀገር ብልጽግና ከማኅበራዊ ኃላፊነት መጎልበት ጋር ከፍተኛ ትሥሥር አለው ሲሉ
ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ::የአንድ ሀገር ብልጽግና ከማኅበራዊ ኃላፊነት መጎልበት ጋር ከፍተኛ ትሥሥር እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “ማኅበራዊ ኃላፊነት ዝቅተኛ የሆነባቸው ሀገራት ለዕድገት ብዙ ማገዶ ይጨርሳሉ” ብለዋል። “የመሠልጠን ጉዟቸውም መሰናክል የሚገጥመው በዋናነት ኃላፊነት ከማይሰማቸው ዜጎቻቸው ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

ዜጎቻችን ማኅበራዊ ኃላፊነት እንዲሰማቸው አርአያ የሚሆኑ ሰዎች ከፊት ከቀደሙ የብልጽግና መንገዱ ቀና ይሆናል ያሉ ሲሆን “አርአያነቱም ከንግግር በዘለለ በተግባር ሲገለጥ የምናስበውን ውጤት በፍጥነት ማሳካት እንችላለን” ሲሉም አስታውቅዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *