loading
የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ

አርትስ ስፖርት 06/03/2011

የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲካሄዱ ካዛኪስታን ከ ላቲቪያ አመሻሽ 12፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡በተመሳሳይ ምሽት 4፡45 ላይ ደግሞ በርካታ ግጥሚያዎች ይደረጋሉ፡፡

በክሮሺያ እና ስፔን መካከል የሚከናወነው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡ ቤልጅየም ከ አይስላንድ፣ ግሪክ ከፊንላንድ፣ ሀንጋሪ ከ ኢስቶኒያ፣ ኦስትሪያ ከ ቦሲኒያ ሄርዜጎቪና፣ ሳን ማሪኖ ከ ሞልዶቫ፣ ሉግዘምበርግ ከ ቤላሩስ እናአንዶራ ከ ጆርጂያ ይጫወታሉ፡፡

በምሽቱ በወዳጅነት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ደግሞ ምሽት 5፡00 ስዓት እንግሊዝ ከ አሜሪካ፤ የዋይኒ ሩኒበክብር የመሸኛ ጨዋታን በዌምብሌይ ስታዲዬም ያከናወናሉ፡፡ በጨዋታው ሩኒ ሶስቱን አናብስት 10 ቁጥርማሊያን በመልበስ በአምበልነት እየመራ ወደ ሜዳ ይገባል ተብሏል፡፡ ጀርመን ከ ሩሲያ፣ ፖላንድ ከ ቼክ ሪፐብሊክ፣የአይርላንድ ሪፐብሊክ ከ ሰሜን አየርላንድ፣ አስራኤል ከ ጓቲማላ እና ኢራን ከ ትሪንዳድና ቶቤጎ በምሽቱ በወዳጅነትጨዋታ ይገናኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *