የአውፓ ህብረት ክሎሮኪን ኮሮናቫይረስን ለማከም ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደ::
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 የአውፓ ህብረት ክሎሮኪን ኮሮናቫይረስን ለማከም ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደ::
የህብረቱ ኮሚሽን ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድሀኒት መጠቀም ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን አባል ሀገራቱ ክሎሮኪን እንዳይጠቀሙ አስጠንቀቋል፡፡የአውሮፓ ህብረት የመድኃኒት ባለሞያዎች ማህበር የአንዳንድ ሀገራት መሪዎች ዜጎቻቸው ረሮሎኪን እንዲወስዱ ሲመክሩ ከመታየታቸው ባለፈ ለኮቪድ 19 ውጤት ይኑረው አይኑረው በቂ ጥናት ተደርጎ ማረጋገጫ አልተሰጠውም ብሏል፡፡እስካሁን ሀይድሮክሲክሎሮኪን ለኮሮና ቫይረስ መድሀኒት ነው በሚለው አቋማቸው የገፉበት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የብራዚሉ አቻቸው ዣየር ቦልሶናሮ ናቸው፡፡ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው ሁለቱ መሪዎች የህክምና አማካሪዎቻቸው ነገሩ ስህተት መሆኑን ደጋግመው ቢነግሯቸውም ሀሳባቸውን ለመቀየር እንደዳልቻሉ ነው የሚነገረው፡፡መድሀኒቱ ከምርምር ባለፈ ጥቅም ላይ እንዳይውል የዓለም ጤና ድርጅት ከአሁን ቀደም የከለከለ ሲሆን የአውሮፓ ህብረትም ይህን ሀሳብ ተቀብሎ ተግባራዊ አድርጎታል፡፡እንግሊዝ ውስጥ የሚታተም የህክምና መፅሄት ተመራማሪዎችን ጠቅሶ ባወጣው ጽሁፍ ክሎሮኪን የወሰዱ የኮቪድ 19 ታማሚዎች የመሞት እድላቸው የሰፋ መሆኑን አመላክቷል፡፡