loading
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባኢንጂነር ታከለ ኡማ አከራዮችን ምሕረት ጠየቁ፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባኢንጂነር ታከለ ኡማ አከራዮችን ምሕረት ጠየቁ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2012 የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአነስተኛ ንግድ የተሠማሩ ነጋዴዎችና ቤተሰቦቻቸው በእንቅስቃሴ መቀነስ እንዳይጎዱ አከራዮች የኪራይ ምሕረት እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል፡፡የጊዜውን ፈተና፣ በጊዜው ብልሃት እና ጸሎት ታግለን ለማለፍ ስንለፋ አንዳንድ የግድ የሆኑ መሠዋዕትነቶች ይደቀናሉ’’ ያሉት ምክትል ከንቲባው አከራዮች ጥቂት የገንዘብ መሠዋዕትነት በመክፈል ሕይወት እንዲታደጉ ጠይቀዋል።

እንቅስቃሴ በመቀነሳችን በተለይ ጥቂት ነገር ሸቅጦ በልቶ ለማደር ደጅ ደጅ የሚያዩ አነስተኛ ንግድ የሚሠሩ ወገኖች ከነቤተሰባቸው በእጅጉ ይጎዳሉ፤ ለእነዚህ እና ተጎዱ ለምንላቸው እስኪ እናስብላቸው፤ ዛሬን ከነልጆቻቸው እንዲያልፉ ማገገሚያ እንዲሆን የኪራይ ክፍያ እንተውላቸው ዘንድ እነሆ ተማፅኖዬ ለአከራዮች ሁሉ ይድረሳችሁ’’ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።አከራዮች ፈጣን አወንታዊ ምላሽ እንደሚሰጡም ተስፋ ማድረጋቸውን ምክትል ከንቲባ መግለጻቸው የከንቲባ ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *