loading
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኃይል ገመድና ኬብል ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኃይል ገመድና ኬብል ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ:: የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች ስርቆት ሳቢያ ተገልጋዮቹ መንገላታታቸውና ኮርፖሬሽኑም ለተደጋጋሚ ኪሳራ መዳረጉን ገለጿል።

የአገልግሎቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሙሉቀን አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች በሌቦች ተቆርጠው በመወሰዳቸው ምክንያት ሰሞኑን ከመሿለኪያ ሚኒሊክ አደባባይ እና ከጦር ኃይሎች ስቴዲየም ያለው መስመር በከፊል አገልግሎቱ ተቋርጧል። እስካሁን 750 የሚደርሱ የኃይል ኬብሎች እና 15 የኃይል ማሰራጫ ገመዶች ስርቆት እንዳጋጠመ የገለጹት ኢንጂነር ሙሉቀንተናግረዋል፡፡ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማበጀት ባለመቻሉ የተነሳ አገልግሎቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *