loading
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ባለፉት አምስት ወራት ያከናወኑዋቸውን ሥራዎች ሊገመግሙ ነው

አርትስ 17/04/11

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ባለፉት አምስት ወራት ያከናወኑዋቸውን ሥራዎች ለመገምገምከዛሬ  ጀምሮ አዳማ ከተማ ከትመዋል፡

የከተማዋ ከንቲባ ፅህፈት ቤት እንደገለፀው  የከተማ አስተዳደሩ በማዕከል፣ በክፍላተ ከተማና በወረዳየሚገኙ ከአንድ ሺሕ በላይ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሚቀጥሉት አራት ቀናት ግምገማዊሥልጠና ያካሂዳል ፡፡

የግምገማዊ የሥልጠናው ዓላማ አዲሱ የከተማው አስተዳደር ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ ኅዳር 30 ቀን2011 ዓ.ም. ድረስ ያከናወናቸውን የለውጥ ሥራዎች አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ መልካም ዕድሎችና መሻሻልያለባቸውን ጎኖች በመገምገም፣ ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች ላይ አቋም ለመያዝ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በቀጣዮቹ ሰባት ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው ለሚከናወኑ ሥራዎች መመርያ እንደሚሰጥመረጃዎች አመልክተዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *