loading
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የኩፍኝ በሽታ የክትባት ዘመቻ ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታዉቋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የኩፍኝ በሽታ የክትባት ዘመቻ ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚካሄድ አስታዉቋል፡፡ቢሮው ዘመቻውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ እድሜያቸው ከ9 ወር እስከ 5 አመት ለሆናቸው ህፃናት ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 2/ 2012 ዓ.ም ክትባቱ ይሰጣል፡፡የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ክትባቱ በተጠቀሱት ቀናት በሁሉም ጤና ተቋማት እና ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡በክትባቱ ወቅት ህፃናት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጂት የተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን በማስከተብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ቢሮዉ ጠይቋል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *