loading
የአዲስ አበባ የወሰን እና ማንነት ጉዳይ በተመለከት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዚማ) የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (አነን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ክርክር አድርገዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 የአዲስ አበባ የወሰን እና ማንነት ጉዳይ በተመለከት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዚማ) የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (አነን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ክርክር አድርገዋል፡፡በአርተስ ቴሌቪዥን የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ  በመቅረብ ሀሳባቸውን የሰጡት ሶስቱ ፓርቲዎች አዲስ  አበባን  በተመለከተ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉባት ከተማ መሆኗን በመግለፅ በተለይም  ከመልካም አስተዳደር እና ከፍተኛ  የሆነ የስራ አጥ ችግር የተንሰራፋባት ከተማ መሆኗን ላይ እንደሚስማሙበት  ነው የገለፁት፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ብልሹ  አሰራር  ምክንያት  ከተማዋ 14 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ በህገወጥ መሬት  ወረራ አጥታለቸ በማለት  የገለፀው  ኢዜማ ለቤቶች  ግንባታ የሚውል 50 ሚሊዮን ብር ተበድሮ አለመመለሱን  ነው የገለፀው፡፡አንደ ኢዜማ እምነት ከሆነ የከተማውን  ብልሹ መዋቅ   መቀየር  ግልፅነትና ተጠያቂነት  ማስፈን  በቀጣይ በስድስተኛው ሀገራዊ  ምርጫ እድሉን ካገኝ በአዲስ አበባ ሊሰራቸው ያቀዳቸው ቁልፍ  ጉዳች  መሆናቸውን ነው ፓርቲው የገለፀው፡፡ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በበኩሉ አዲስ አበባ 122ሺ ሄክታር መሬት  የነበራት ከተማ መሆኗን በማስታወስ አዲስ አበባ ከተማ  ያለባትን የመልካም አስተዳደር ችግር በመቅረፍ እራስ ገዝነቷነን በማጠነከር የቤት ፈላጊውን ጥያቄ ለመመለስ 1 ነጥብ  2 ሚሊዮን ቤቶች ለመገንባት ማቀዱን ነው የተናገረው፡፡

እንደ ኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ  እምነት  አንቀስ 49  ንኡስ አንቀፅ 5 ተግባር ላይ እያዋለ አይደለም በማለት  አሁንም በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ አዋሳኝ ድንበሮች አሁንም ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጧል፡፡ (ኦነን)  አዲስ አበባ  አሁንም ለአሮሚያ ክልል የካሳ ክፍያ መክፈል አለባት፤ ፓርቲው በምርጫው ዕድሉን ካገኝ የአዲስ አበባን ልዩ ጥቅም ከኦሮሚያ ማግኝት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ነው ያስታወቀው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *