loading
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለህብረቱ ስብሰባ እና ለታላቁ ሩጫ የሚዘጉ እና አማራጭ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ

አርትስ 07/03/2011
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሀዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንደገለፁት
ከፓርላማ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣መስቀል አደባባይ፣ፍላሚንጎ፣ ኦሎምፒያ፣ ወሎሰፈር፣ ፍሬንድ
ሺፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድ፣ኤርፖርት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን መኪና ማቆምም አይቻልም
ብለዋል፡፡
ከፓርላማ መብራት በቤተመንግስት ፍልውሃ ብሄራዊ ቲያትር ሜክሲኮ አደባባይ በህብረቱ አዳራሽ ዙሪያ
የሚዘጋ ሲሆን ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኢምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ያለው መንገድ ላይም
ተሸከርካሪ ለአጭርም ለረዥምም ሰዓት መቆም የማይቻል መሆኑ ተነግሯል፡፡
ጉባኤው እና ሩጫው እስኪጠናቀቅ ማህበረሰቡ አማራጭ መንገዶችን መጠቀም ይችላል ያሉት
ምክትል ዳይሬክተሩ ፤በዚህም መሰረት ከጦር ሃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ እና መገናኛ
የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች በኮካ ድልድይ በአብነት ተክለሃይማኖት ወይም በባልቻ ሆስፒታል አረቄ ፋብሪካ
ጎማ ቁጠባ ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን በንግድ ማተሚያ አሮጌ ቄራ መንገድ መጠቀም ይታላል
ተብሏል፡፡
ከሳር ቤት ጎፋ ማዞሪያ ቄራ ጎተራ ቦሌ ሚካኤል ሩዋንዳ አትላስ በዘሪሁን ህንፃ አድርገው መሄድ
እንደሚችሉ የተነገረ ሲሆን የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች ደግሞ በአትላስ ዘሪሁን፣ከቦሌ ሚካኤል
ወደጎተራ ፣ ቀለበት መንገድ መገናኛ በእንግሊዝ ኢምባሲ፣ በቀለበት መንገድ መገናኛ አድዋ አደባባይ
በአቧሬ አራት ኪሎ እና ከፍላሚንጎ ደምበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መጠቀም እንደሚቻል
ሰምተናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *