loading
የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር የሚዘልቅ ነው ሲሉ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር የሚዘልቅ ነው ሲሉ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ገለፁ::

እየተገነባ ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር ዘላቂነት ያለው ነው” ሲሉ በሠራዊቱ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ተናገሩ።ሜጄር ጄኔራሉ ሠራዊቱ በሰው ኃይል ስብጥርና በአመራር አደረጃጀቱ ለውጥ ማምጣቱን ጠቅሰዋል።

ከቁጥር አንፃር ሚዛናዊ የሆነ ስራ መስራትና ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የሚወክል በማድረግ ረገድ ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ያብራሩት።እንደ ሜጀር ጄኔራል ሹማ ገለጻ ሠራዊቱ ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ነፃ ሆኖ አገራዊ ተልዕኮውን የሚወጣበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

ሠራዊቱን በአዲስ መልክ ከማጠናከር ስራው ጋር ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የአመለካከት ለውጥ ማምጣት፣ አደረጃጀቱን ፈጣንና ቀልጣፋ ማድረግ፣ ደረጃውን የጠበቀ የተግባር ስልጠናና ብቃት ማሟላትና ዓለም በደረሰበት ቴክኖሎጂ ልክ ትጥቅ እንዲኖረው ማድረግን ጠቅሰዋል።በዚህ ረገድ ሠራዊቱ የአገር ሉዓላዊነት፣ ሠላምና መረጋጋትን ማስጠበቅ በሚችልበት ደረጃ ላይ መሆኑን ሜጀር ጄኔራሉ ተናግረዋል።

የአሸባሪነት ተግባር በዓለም መስፋፋት ዋነኛ የሠላም እጦት ምክንያት እየሆነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በስልጠናዎች የዳበረና ብቃት ያለው ሠራዊት የመገንባት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏልም ብለዋል።ለዚህም ኢትዮጵያ አዲስ ካቋቋመችው የባሕር ኃይል ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ ኃይል መዘጋጀቱን ነው የገለፁት።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *