loading
የአፋር ክልል ነዋሪዎች የባቡር መስመር ዝርጋታው በቂ መተላላፊያ ስለሌለው ካሳ ይከፈለን አሉ

አርትስ 15/02/2011

የአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር መስመር ለሰዎችና ለእንስሳት በቂ መተላላፊያ የሌለው በመሆኑ ተገቢው ካሳ ይከፈለን ሲሉ የአፋር ክልል ነዋሪዎችጠይቀዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ለመሸጋገሪያ የሚሆን በቂ ማቋረጫ ባለመኖሩ ህብረተሰቡ  በተለይም አቅመ-ደካሞች እየተቸገሩ ነው።

ይህም በሽተኞችና ነፍሰጡር እናቶች በቀላሉ የአምቡላንስ አገልግሎት እንዳያገኙ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በበኩሉ ከክልሉ አመራሮችና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ችግሩን ለመፍታት እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

የአዋሽ-ኮምቦልቻ 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ግንባታ በ2007 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረ ሲሆን እስካሁን አልተጠናቀቀም።

የባቡር መስመሩ የአፋርና አማራ ክልል ህዝቦችን ሁለንተናዊ ትስስር ለማጎለበት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *