የአፍሪካ ህብረት እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጎን ለጎን እንዲውለበለቡ ረቂቅ ተዘጋጀ
የአፍሪካ ህብረት እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጎን ለጎን እንዲውለበለቡ ረቂቅ ተዘጋጀ
አርትስ 13/03/2011
የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት እ.ኤ.አ ሜይ 25 ቀን 2013 በደቡብ አፍሪካ ሲከበር አባል ሀገራቱ ከየራሳቸው ሰንደቅ አላማ ጎን ለጎን የአፍሪካ ሕብረትን ሰንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ ከማድረግ በተጨማሪ መዝሙሩ እንዲዘመር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር የውጭ ጉዳይሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውሷል፡፡
ቃል አቀባዩ አቶ መለስ አለም የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ማድረጉ አፍሪካዊያን ወንድሞች ኢትዮጵያን እንደ ሀገራቸው እንዲሁም አዲስ አበባን እንደ መዲናቸው እንዲያዩዋት ያደርጋል ብለዋል፡፡
ይህ እንዲሆን ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጣይ ይቀርባል ያሉት አቶ መለስ ከመፅደቁ በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መድረኮችን በማዘጋጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ይካሄዳል ብለዋል፡፡
አንድ አንድ የህብረቱ አባል ሃገራት ባንዲራውን እያውለበለቡ ነው፤የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበትን ቀንም እንደ ብሄራዊ በዓል የሚያከብሩ አሉ ብለዋል፡፡
በሌላ ዜና የኢትዮጵያና የቻይና የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑ ታውቋል፡፤ በፎረሙ 100 አባላትን የያዘ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ በፎረሙ የኢንቨስትመንት ተቋማትና የግል ባለሃብቶች ይሳተፋሉ፤60 የሚሆኑ ኩባንያዎችም እንደሚገኙ ከቃል አቀባዩ ሰምተናል፡፡