የኢሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዕጣ ድልድል ይፋ ሆነ
የኢሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዕጣ ድልድል ይፋ ሆነ
የ2018/19 በ16 ቡድኖች መካከል የሚደረገው የኢሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች የዕጣ ድልድል ይፋ ሁኗል፡፡
የዕጣ ድልድሉ ዛሬ ከስዓት በኋላ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር መቀመጫ ሲውዘርላንድ ኒዮን ይፋ የሆነ ሲሆን እንግሊዝን የሚወክሉት አርሰናልና ቼልሲ ቀለል ያለ ተጋጣሚ ደርሷቸዋል፡፡
በድልድሉ መሰረት የኡናይ ኢመሪው አርሰናል ከፈረንሳዩ ሬን ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡ መድፈኞቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ኤመሬትስ ላይ ያደርጋሉ፡፡
ሌላኛው እንግሊዝ ቡድን ቼልሲ ከዩክሬኑ ክለብ ዳይናሞ ኬቭ ጋር ተደልድሏል፡፡ ሰማያዊዎቹ በዚህ ግንኙነት የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን ሜዳቸው ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ያከናውናሉ፡፡
በሌሎች የዕጣ ድልድል የኢሮፓ ሊግ ቀበኛው የስፔኑ ስቪያ ራሞን ሳንቼዝ ፒዡዋን ላይ የቼኩን ስላቪያ ፕራህን የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡
የጀርመኑ አይንትራክት ፍራንክፉርት ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር ሲጫወት፤ ሌላኛው የጣሊያን ወኪል ናፖሊ ደግሞ የኦስትርያውን አር. ቢ ሳልዝበርግ ይገጥማል፤ የስፔኑ ቫሌንሲያ ሜስቲያ ላይ ከሩሲያው ክራስኖዳር ጋር ይፋለማል፡፡
የክሮሽያው ዲናሞ ዛግሬብ ከፖርቱጋሉ ቤንፊካ፤ የሩሲያው ዜኒት ፒተርሰበርግ ከስፔኑ ቪያሪያል ጋር እንዲጫወቱ ተደልድለዋል፡፡
የዚህ ዙር የመጀመሪያ ግጥሚያዎች ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡