የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ መነሳቱ ለቀጠናው ሀገራት ግንኙነት መጠናከር ሚናው የጎላ ነው አለ
አርትስ 06/03/2011
የኢትዮጵያ መንግስት እንዳለው የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስታት (ኢ.ጋ.ድ) አባል ሀገራት ማዕቀቡእንዲነሳ ላደረጉት አስተዋፅኦና ላሳዩት ትብብር አድናቆቱን ገልጧል፡፡
15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ሰኞ ዕለት ማእቀቡን ለማንሳት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ የማንሳትረቂቁም በእንግሊዝ መንግሥት አማካኝነት እንደቀረበ ተገልጿል። በትናንትናው ዕለትም የጸጥታው ምክር ቤትባካሄደው ስብሰባ ማዕቀቡ ተሸሯል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ኤርትራ ላይ ማዕቀብ የተጣለው ለአልሻባብ ድጋፍ ያደርጋልበሚል ነበር፤ ከዚህ በፊት በመሳሪያ ዝውውር፣ የባለስልጣናት ጉዙና የንብረት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩ ማዕቀቦችመጣላቸው የሚታወስ ነው፡፡
የማዕቀቡ መነሳትም በአፍሪካ ቀንድ ለሚታየው መረጋጋትና ሰላም እንዲሁም ለቀጠናው ግንኙነት መጠናከርአስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል፤ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ትስስርየበለጠ ያጠናክረዋል ሲል የጠቅላይ ሚስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡