
የኢትዮጵያ መንግስት ከዋና ዋና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ስምምነት ላይ ደረስኩ አለ::
ስምምነቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት፣ ከህብረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበትና ዘላቂ ኑሮ የሚመሩበትን ሂደት ለመፈጸም የሚያስችል ነው ተብሏል።
በስምምነቱ መሰረት በጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ውስጥ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤትም ተቋቁሟል::
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፕሮጀክቱን ጽሕፈት ቤት እንዲመሩ አቶ ተስፋዬ ይገዙን መሰየማቸውን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል።