
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሀላፊነታቸው ተነሱ
አርትስ 22/01/2011
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ብርሐኑ በሻህ ከነበሩበት ኃላፊነት እንዲነሱ በግል ፍላጎታቸው ለኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ቦርድ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ከትናንት ጀምሮ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከሀላፊነት በግል ፈቃዳቸው ተነስተዋል፡፡
በምትካቸውም ኢ/ር የኋላሽት ጀመረ የኮርፖሬሽኑ ተወካይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል፡፡