loading
የኢትዮጵያ ሳምንት ከግንቦት 10 እስከ ግንቦት 16 በወዳጅነት ፓርክ ይከበራል::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የኢትዮጵያ ሳምንት ከግንቦት 10 እስከ ግንቦት 16 በወዳጅነት ፓርክ ይከበራል:: ሀሳቡን ያመነቨጩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ሳምንት የሚለውን ዝግጅት እንዲያስተባብሩ ለሦስት ሴት ሚኒስትሮች የቤት ሥራ ሰጥተዋቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት ስራውን በሃላፈነት የተረከቡት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሣው፣ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እና የሴቶች፣ ወጣቶች እና ሕፃናት ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ ዝግጅቱን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የዝግጅቱ ዓላማም ሀገሪቱ ያላትን ሀብት እና የተፈጥሮ ፀጋ በማስተዋወቅ ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር ነው ተብሏል፡፡ ፌስቲቫሉ ሁሉም ክልሎች ያሏቸው ልዩ መገለጫዎችና የተፈጥሮ ሃብቶች በተለያዩ ቅርፃቅርፆች፣ በሥዕል እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ምሥል በወዳጅነት አደባባይ ለእይታ መዘጋጀታችን ሚኒስትሮቹ
ተናግረዋል፡፡ ከዝግጅቱ የሚገኘው ገቢም ለተፈናቃይ ዜጎች ማቋቋሚያ እንደሚውልም ጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ተመልክቷል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *