loading
የኢትዮጵያ ሽልማት በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013  በዓለም ፀሐይ ወዳጆ የጥበብ መድረክ አዘጋጅነት ከዚህ በፊት በአሜሪካ ለሶስት ዙር የተካሄደው የኢትዮጵያ ሽልማት ለአራተኛ ግዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በጥር 2011 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ኮሎራዶ የተቋቋመው ዓለም ፀሐይ ወዳጆ የጥበብ መድረክ ለመጀመርያ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ሄልተን ነሀሴ 29፣ 2013 ዓ.ም በዕለተ ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ታዉቋል፡፡ ሽልማቱ ለሀገር ለጥበብ እና ለወገን አስተዋፅኦ ላደረጉ የሚሰጥ ነው የተባለ ሲሆን፤ በጥበብ መድረኩም ጸኃፌ ተዉኔት ፣መምህር ፣ገጣሚና ደራሲ አያልነህ ሙላት፤አንጋፋ ድምጻዊያን አስቴር አወቀ እና ዓለማየሁ እሸቴ ገጣሚና የዜማ ደራሲ ሞገሥ ተካ ታዋቂ ሰዎች አድናቂዎቻቸዉ እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት የኢትጵያ ሽልማት ይበረክትላቸዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪ ወጣቶች ለአርዓያነታቸው እና ለጅምራቸው የማበተራታቻ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ፣ ድምጻዊትና ተወናይት ሳያት ደምሴ፣ ተዋናይና ገጣሚ ተስፋሁን ከበደ እና ድምጻዊ ዳዊት ጽጌ ተሸላሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የተሰኘዉን ሽልማት የተበረከተላቸው የጥበብ ንግሰት ዓለምፀሐይ ወዳጆ ድምጻዊ አያሌዉ መስፍን እና ሳይንቲስት ዶ/ር አበራ ሞላ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *