loading
የኢትዮጵያ ባንኮች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያለባቸውን የቦታ ችግር እንዲቀርፍላቸው ጠይቁ

የኢትዮጵያ ባንኮች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያለባቸውን የቦታ ችግር እንዲቀርፍላቸው ጠይቁ

ባንኮቹ ጥያቄያቸዉን ያቀረቡት የባንክ ብሬዝዳንቶች ከከንቲባ ታከለ ኡማ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነዉ ፡፡

በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ 16 የግል እና 2 የመንግስት ባንክ አመራሮች ከከንቲባዉ ጋር ባደረጉት ዉይይት የከተማ አስተዳደሩ ያለባቸውን የቦታ ችግር እንዲቀርፉ ጠይቀዋል።

ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ባገኘነው መረጃ ተቋማቱ የሚጠበቅባቸውን ማህበራዊ ሀላፊነት ለመወጣት እና አስፈላጊ በሆነው ሁሉ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በተለይም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *