የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወሰነ::
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወሰነ::
ቦርዱ ይህን ውሳኔ ያለፈው በአንደሰንድ የምጫ ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶች መራዘሙን መነሻ በማድረግ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በዚህም መሰረት በምእራብ፣ በምስራቅ ወለጋ እንዲሁም በቄለም ወለጋና በሆሮጉድሩ ዞኖች 31 ምርጫ ክልሎች መካከል በ24ቱ ምዝገባው ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን ወስኗል። በሌላ በኩል በበኔኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል በከማሽ ዞን ከሚገኙት አምስት የምርጫ ክልሎች በአራቱ የመራጮች ምዝገባ በነዚሁ ቀናት እንዲከናወን ተወስኗል፡፡
በጸጥታ ችግር የተነሳ የመራጮች ምዝገባ ሳይከናወንበት የነበረው የአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዪ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ የመራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 29 – ግንቦት 13 ቀን 2013 ድረስ ይከናወናል። በመሆኑም ፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያ እና ሲቪል ማህበራት የመራጮች ምዝገባን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን መረጃን በመስጠት እና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ
አቅርቧል፡፡