loading
የኢትዮጵያ አየርመንገድ ተጠሪነቱ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ሆነ

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ተጠሪነቱ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ሆነ

አርትስ 20/02/2011

 

በትራንስፖርት ሚኒስቴር ስር ከነበሩ ተቋማት አንዱ የነበረውና ላለፉት አመታት ተጠሪነቱ ለዚሁ መስሪያ ቤት የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ተጠሪእንዲሆን ተደርጓል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ እንደተመለከተው አየር መንገዱ በመንግስት ልማት ይዞታ አስተዳደር ኤጀንሲ ተቋም ስር ሆኖ ተጠሪነቱ ግንለገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር እንዲሆን ተደርጓል፡፡

እንደሚኒስትሯ መረጃ በአሁኑ ወቅት የትራንስፖርት ሚኒስትር በስሩ የሚመራቸው ተቋማት 10 ሆነዋል።

የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣን፣ ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ የክፍያ እና መንገዶች ኢንተርፕራይዝ፣ የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት፣ መድን ፈንድ አስተዳደር፣ የሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን፣ የማሪታይም ጉዳዮችባለስልጣን፣ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር እና የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚኒስትሩ ስር የተካተቱ ተቋማት ናቸው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *