የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙሉ ለሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ ዳግም ሊያደርግ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙሉ ለሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ ዳግም ሊያደርግ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ ወደ ኖርዌይ ኦስሎ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በረራው በዚህ ዓመት በሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ከአዲስ አበባ በመነሳት መዳረሻውን ስቶክሆልም ኦስሎ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በረራው ታሪካዊ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን የአውሮፕላኑ አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጅ እና መላው ሰራተኞች በኢትዮጵያውያን ሴቶች ሙሉ በሙሉ የሚመራ ነው ተብሏል፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በሁሉም የበረራ ዘርፍ ብቁ የሆኑ ሴቶች ተቋሙ ስላለው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አየር መንገዱ ከዚህ ቀደምም በሴት አብራሪዎችና የበረራ ቡድን ብቻ የተመራ በረራ ማድረጉ ይታወሳል።